ከሀዋሪያቱ በኃላ ለምን አልቀጠለም የሀዋሪያነት አገልግሎት ለምንስ በዚህ ዘመን ሀዋሪያት የሉም እንላለን?
By Augsburg Catholic
ከሀዋሪያቱ በኃላ ለምን አልቀጠለም የሀዋሪያነት አገልግሎት ለምንስ በዚህ ዘመን ሀዋሪያት የሉም እንላለን?
1. የሀዋሪያነት ሹመት ወይም ስልጣን የተሰጠው ለደቀመዛሙርቱ ብቻ ነበር ወንጌልን እንዲሰብኩ ቤተክርስቲያንን እንዲተክሉ ስልጣን የተሰጠው ለሀዋሪያቱ ብቻ ነበር ::
ቆላስይስ 1:23
23 ይህም፥ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ፥ በሃይማኖት ጸንታችሁ ብትኖሩ ይሆናል። ያም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፥ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።
2. ሀዋሪያቱ የተሾሙት በቀጥተኛ ጥሪ ያም በክርስቶስ ነበር :: ማቲያስ ሲመረጥ በይሁዳ ቦታ ሀዋሪያቱ ለጌታ ውሳኔውን በመተው ማቲያስ ላይ እጣው እንደወደቀ እናያለን :: ጳውሎስም እንደዚሁ በክርስቶስ እንደተመረጠ ሐዋ 9:3-16 ባለው ክፍል ማየት እንችላለን::
ገላትያ 2:7-9
7 ተመልሰው ግን ጴጥሮስ ለተገረዙት የሆነው ወንጌል አደራ እንደ ተሰጠው እንዲሁ ለእኔ ላልተገረዙት የሆነው ወንጌል አደራ እንደ ተሰጠኝ አዩ፤
8 ለተገረዙት ሐዋርያ እንዲሆን ለጴጥሮስ የሠራለት፥ ለእኔ ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ እንድሆን ሠርቶአልና።
9 ደግሞ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ እነርሱም ወደ ተገረዙት ይሄዱ ዘንድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤
ሀዋሪያቱ አስራ ሁለቱ የተጠሩበትን አጠራር immediate call ስንለው የጳውሎስን እና የማቲያስን ደሞ extraordinary call እንለዋለን እነዚህን ሁለቱን በዚህ ዘመን አናያቸውም ምክንያቱም immediate call አለ እንዳንል ክርስቶስ በሰማይ ነው ልክ አስራ ሁለቱ እንደተመረጡት በዚህ ዘመን ሊሆን አይችልም extraordinary call ቢሆን በዚህ ዘመን አናየውም ሀዋሪያቱ ከሞቱ በኃላ የተነሳ የነሱ ተተኪ የሆነ አንድም ሀዋሪያ ስለሌለ :: ሀዋሪያቱ ፕሬስቢተሮችን ሽማግሌዎችን ነው ትተውልን የሄዱት ::
ቲቶ 1:5
5 ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤
ቆላስይስ 1:23
23 ይህም፥ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ፥ በሃይማኖት ጸንታችሁ ብትኖሩ ይሆናል። ያም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፥ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።
3. የሀዋሪያቱ ዶክትሪን የማይሳሳት ነበር ከጌታ ስለተቀበሉት የተለየ ነገር ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ተቃርነው አልሰበኩም ለዛ ነው
ኤፌሶን 2:20
20 በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
ሲሰብኩ ስለ ነበረውም ቃሉ እንዲህ ይላል
ገላትያ 1:8-9
8 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።
9 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።
1 ዮሐንስ 1:1-3
1 ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመ7ሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤
2 ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤
3 እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።
4. ታምራት ማድረግ
ሀዋሪያቱ ታምር የማድረግ ሀይል እንደነበራቸው ቃሉ ይነግረናል:: ሀዋሪያ ለመባልም ምልክት ያስፈልግ እንደነበር ቃሉ ይነግረናል::
ማቴዎስ 10:1
1 አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው።
2 ቆሮንቶስ 12:11-12
11 በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ፤ እናንተ ግድ አላችሁኝ፤ እናንተ እኔን ልታመሰግኑ ይገባ ነበርና። እኔ ምንም ባልሆን እንኳ፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አልጎድልምና።
12 በእርግጥ የሐዋርያነት ምልክት በመካከላችሁ በምልክትና በድንቅ ነገር በተአምራትም በሁሉ ትዕግሥት ተደረገ።
5. ወንጌልን መስበክ
የሀዋሪያቱ አገልግሎት በቦታ የተገደበ አልነበረም:: ስልጣን እና ትእዛዝ የተቀበሉት ወደ አለም ሀሉ ወደ ሁሉም ቦታ እንዲሄዱ ነበር::
ማቴዎስ 28:19-20
19-20 “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
ማርቆስ 16:15
15 እንዲህም አላቸው፦ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፡ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
አሁን ግን ቤተክርስቲያን ተተክላለች ሀዋሪያት ጳጳሳት ሰባኪያን ሽማግሌዎች በሾሟቸው ሰዎች አማካኝነት አገልግሎት ቀጥሏል::
ሐዋ. ሥራ 14:23
23 በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው።
ሐዋ. ሥራ 20:28
28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
ቲቶ 1:5
5 ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤
1 ጴጥሮስ 5:2
2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
6. ክርስቶስን በስጋ ማየት ወይም ሞቱን ማየት
ማቲያስ ሲመረጥ ሌሎቹ ሀዋሪያት መስፈርታቸው ይሄ እንደነበር ቃሉ ይነግረናል::
ሐዋ. ሥራ 1:21-22
21-22 ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል።”
ሐዋ. ሥራ 10:41
41 ይኸውም ለሕዝብ ሁሉ አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተመረጡ ምስክሮች ለሆንን ለእኛ ነው እንጂ፤ ከሙታንም ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን።
ስለዚህ ከላይ በዘረዘርናቸው 6 ምክንያቶች በዚህ ዘመን ሐዋርያ ነኝ የሚል እነዚህን መስፈርቶች ስለማያሟላ ተመዝኖም ስለሚወድቅ ሀዋሪያት ይሄን ሀዋሪያ ሾመንላችኃል ሳይሆን ሰባኪያንን መምህራንን ጳጳሳትን ሽማግሌዎችን ነው ሾመውልን የሄዱት ስለዚህ ከነሱ በኃላ የተነሳ ሀዋሪያ የለም:: መጨረሻ የሞተው ሀዋሪያ ዩሐንስ ነው በራእይ መጽሀፉ እንዲህ ይላል
ራእይ 21:14
14 ለከተማይቱም ቅጥር አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፥ በእነርሱም ውስጥ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።
ከነዚህ ምክንያቶች የተነሳ ሀዋሪያ በዚህ ዘመን የለም ብለን መደምደም እንችላለን::
1 ዮሐንስ 4:1
1 ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።