ቤተእምነት አልባነት (Non denominationalism)
By Addisu Bekele
ቤተእምነት አልባነት (Non denominationalism)
ቤተእምነት አልባነት (Non denominationalism) ማለት ወጥ የሆነ አንድ ቤተእምነት የሌለው፥ ወጥ ሆነ የአስተምህሮ፥ ወጥ የሆነ አስተምህሮ ስለሌለው የስህተት አስተምህሮ የምለውም የለውም። ይህ ቤተእምነት አልባነት ከላይ የምቆጣጠረው አካል አይኖረውም። የአምልኮ ሥርዓት ይሁን፥ የአስተምህሮ ጉዳዮችን የቤተክርስቲያኑ ፓስተር ደስ እንዳለው ይወስናል። ደስ ካለው እኔን አምልኩኝ ልል ሁላ ይችላል። ከዚህ የተነሳ ሥልጣን ሁሉ በፓስተሩ እጂ ይወድቃል። (Unlimited power) ተጠቃሚ ይሆናል። በዚህ በቤተእምነት አልባነት የተጠቁ ሰዎች፦ ቤተእምነታዊ የሆኑ ሰዎችን ሐይማኖተኞች እያሉ ያፌዛሉ፥ ከአፋቾ ሐይማኖት ወደ እግዚአብሔር መንግስት አያስገባም፥ አስተምህሮን አትስበኩ ኢየሱስን ስበኩ፥ አስተምህሮ ወደ እግዚአብሔር መንግስት አያስገባም የምሉ ቃላቶች አይጠፉም። ምንም በመጽሐፍ ቅዱስ የተደራጀ አስተምህሮ የላቸውም፥ ለአስተምህሮም ይሁን ለአምልኮ ወጥና ቋም ሥርዓት የላቸውም።
ፓስተሩ ደስ እንዳለው ይለዋውጣል። አብዛኛውን ጊዜ ኢየሱስ ጌታ ነው፥ መንፈስ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ስሉ ብቻ ታገኛላችሁ። በጣም ስሜታዊና ትዕቢተኞች ናቸው። ያልታወቅ ኢ-አቃፍነት (hidden exclusivest) ናቸው። በጣም ከእነርሱ አስተሳሰብ ውጭ የሆነውን ይጠላሉ፥ ትዕቢተኞች ናቸው፥ ፍቅር ያላቸው ይመስላሉ በጣም በጥላቻ የተሞሉ ናቸው። ሁሉም እንደ እነርሱ እንዲያስቡ ይፈልጋሉ። ከዚህ የተነሳ በጥላቻና በትዕቢት የተሞሉ ይሆናሉ። ኢ-አቃፍ ናቸው። ለtraditionu ምንም ቦታ የላቸውም። በSolo scripture የምመሩ ናቸው።
እንግዲህ አሁን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን የተቆጣጠረው ይህ ይመስለኛል። በኢትዮጵያ ይህ የቤተእምነት አልባነት (Non denominationalism) ተቆጣጥረዋል። አንድ ወጥ የሆነ ድንበር የለም። አጥቢያዎቹ እንደፈለጉ ይመራሉ። እንግዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ Non denominational ያልሆነች ቤተክርስቲያን ያለ አይመስለኝም። መካነ ኢየሱስ፥ ቃለ ሕይወት ምናምን ልትሉ ትችላላችሁ። በሚያሳዝን መልኩ እነርሱም ለቤተእምነት አልባነት ተጋልጠዋል። ለምሳሌ ከመካነ ኢየሱስ ልነሳ። መካነ ኢየሱስ በጣም ድንቅ የሆነ መዋቅር ያላት ቤተክርስቲያን ነች፥ መዋቀሯ ለመቆጣጠርም በጣም ምቹ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ይህ መዋቀር እየሰራ አይደለም። ጽሕፈት ቤቱ ሲኖዶሶችን አይቆጣጠርም፥ ሲኖዶሶቹ ሰባካን አይቆጣጠሩም፥ ሰበካ ማህበረ ምዕመናኖችን አይቆጣጠርም ምናልባት ሰበካው በሁለት ዓመት አንደ ብቻ ወደ ማህበረ ምዕመናኖቹ ይመጣሉ። እርሱንም ምርጫ ስደረግ ብቻ።
ስለዚ ማህበረ ምዕመናኖቹ እንደፈለጉ ይሆናሉ። (ስለ መካነየሱስ መዋቅር ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለሳለሁ) የቤተክርስቲያን ሥርዓት የምባል ነገር አይታሰብም፥ ምናልባት አንዱ ደስ ካለው ተነስተው እኔ በስላሴ አላምንም፥ ድኅነት በኢየሱስ ብቻ አይደለም፥ ኢየሱስ አምላክ አይደለም ልል ይችላል። ብኖርም የሚያወግዝ የለውም ደስ ያለውን ያምናል፥ ደስ ያለውን ያደርጋል። እስከ አሁኑ በኢትዮጵያ ፕሮቴስታንት ታርክ አንድ ሰው ተወግዘው ያውቃል? አይታወቅም። በቤተእምነት አልባነት ውስጥ ወግዘት የምባል ነገር የለማ። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን በቤተእምነት አልባነት (Non denominationalism) ሥር ወድቀዋል።
የቤተእምነት አልባነት ችግሮች (Problems of non denominationalism)
አስተምህሮ አልባነት (Non doctrine) ይሆናል። ወጥ የሆነ ቤተእምነት ከለሌለው ወጥ የሆነ አስተምህሮ አይኖረውም። ፓስተሩ ደስ ያለውን መርጦ ይህ የእኛ አስተምህሮ ነው ብለው ይወስናል። ወጥ የሆነ አስተምህሮ ከሌላቸው ደግሞ ወጥ የሆነ የስህተት አስተምህሮ አይኖራቸውም።
ሁለተኛ ሥልጣኑ ተጠቃሎ በፓስተሩ እጂ ይወድቃል። ተጠያቂነት አልባ ይሆናሉ። (Lack of accountability) ፓስተሩ ከላይ የምጠይቀው አካል አይኖረውም እንደፈለገ ይወስነዋል፥ ገንዘቡም፥ አባሎቹም፥ ቤተክርስቲያኑም የግሉ ይሆናል። ማንም የሚጠይቀው አይኖረውም። በዛው ልክ ፓስተሩ በማነኛውም ጉዳይ ላይ እንደፈለገ ይወስናል።
ሦስተኛው ነገረ መለኮት አልባ ይሆናል (Lack of Theology) በዚህ በቤተእምነት አልባነት ውስጥ ነገረ መለኮት ለጉድ ይፈራል። ነገረ መለኮት አይታሰብም። ሰው ደስ ያለውን ያደረጋል፥ ደስ ያለውን ያምናል። አብዛኛውን ጊዜ ኢየሱስ፥ ኢየሱስ፥ መንፈስ ቅዱስ፥ መንፈስ ቅዱስ፥ ኢየሱስ ጌታ ነው ምናምን የምሉ ቃላትን ብቻ ታገኛላችሁ። ኢየሱስ ጌታ ነው ስል ምን እያለ እንደሆነ ራሱ አያውቅም። ስለዚህ ወጥ የሆነ ነገረ መለኮት አይኖራቸውም።
አራተኛ ለግላዊ መጽሐፍ ቅዱስ ሥነ አፈታት የተጋለጠ ይሆናል (vulnerable to subjective interpretation of the Bible.) ወጥ የሆነ ሥነ አፈታት አይኖራቸውም አንድ ግለሰብ እንደፈለገ፥ እንደመጣለት ይተረጎማል። ይህ ቀጣም አደገኛና ለሐሰት አስተምህሮ ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። ከዚህ የተነሳ They're vulnerable to heresy ሁልጊዜ ለስህተት አስተምህሮና ለስህተት ልምምድ ተጋላጭ ናቸው።በአጠቃላይ ይህ ቤተእምነት አልባነት (Non denominationalism) ዘርፈ ብዙ ስህተት አለው።
Comments
Log in to join the conversation.
Log InNo comments yet — be the first to share your thoughts.